1 ሐንቲሊ1 ሐንቲሊ ክ1507-1491 ዓክልበ. አካባቢ ከንግሥቱ ሐራፕሺሊ ወንድም 1 ሙርሲሊ በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ ነበር። የሐንቲሊና የባለቤቱ የሐራፕሺሊ ሴት ልጅ ደግሞ የዚዳንታ ሚስት ነበረች። ንጉሡ ሙርሲሊ የማርዱክን ጣዖት ይዞ ከባቢሎን ዘመቻው በተመለሰበት ጊዜ፣ «የዋንጫ ተሽካሚ» ሐንቲሊና የልጁ ባል ዚዳንታ በሤራ ገብተው ሙርሲሊን ገደሉና ሐንቲሊ ያንጊዜ የኬጥያውያን ንጉሥ ሆነ። በኋላ ንጉሡ ቴሌፒኑ በጻፈው የቴሌፒኑ ዐዋጅ በተባለው ሰነድ የሐንቲሊ ዘመን ይተረካል፤ ሐንቲሊ ንጉሡን ሙርሲሊን በሤራ ስለ ገደለው አሁን እሱ ንጉሡ ለራሱ ሕይወት ፈራና ጸጸተ ይላል። ከዚያም፦
ከርከሚሽ በሶርያ ሲሆን ከዚያ ዙሪያ ሑራውያን ወይም ሚታኒ ጋር እንደ ታገለ ይመስላል። ኪዙዋትና (የበኋላ ኪልቅያ) የኬጥያውያን ክፍላገር ሆና እንደ ቀረች ይታመናል። በኋላ በ4 ቱድሐሊያ (1249-1217 ዓክልበ.) ጽላት ዘንድ፣ የካስካውያን ብሔር በስሜኑ በጥቁር ባሕር ላይ መጀመርያ የታዩ በዚህ 1 ሐንቲሊ ዘመን የተቀደሠውን ከተማ ኔሪክን ሲያጥፉ ነበር። ይችም ከተማ እስከ 1275 ዓክልበ. ድረስ ዳግመኛ አልተሠራችም ይላል። የሐንቲሊን ወራሾች ገድሎ ዚዳንታ በሐቲ ዙፋን ላይ ተከተለው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ዚዳንታ በገዛ ልጁ አሙና ተገደለ፤ አሙናም የኬጥያውያን ንጉሥ ሆነ። የዚዳንታ ሚስት የሐንቲሊ ሴት ልጅ ስለ ሆነች ይህ አሙና የሐንቲሊ ልጅ ልጅ እንደ ነበር ይታስባል።
|